Available Courses
|
መሓሪ የትምህርት አገልግሎት ዓላማው የሥነመለኮት ትምህርቶችን በአማርኛ ማስተማር ነው። በጠቅላላው ሰላሳ አንድ ትምህርቶችን የምናስተምር ሲሆን ተማሪዎች በቅደም ተከተል እንደቀረበው ከእነዚህ ትምህርቶች በአንዱ ይመዘገባሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ተማሪዎች ሌሎችን ትምህርቶች ለመማር ከመመዝገባቸው በፊት የመጀመሪያዎቹን ሦስት መሠረታዊ ትምህርቶች መማር ይኖርባቸዋል፡፡ ለመመዝገብ የአንድ ጊዜ ምዝገባ ክፍያ $25 እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኮርስ $50 እናስከፍላለን። ከአሜሪካ ካናዳና አውሮጳ ውጭ የምትኖሩ ከሆነ ጻፉልንና በስኮላርሺፕ የምትማሩበትን ሁኔታ እናመቻቻለን። ተማሪዎችን ስፖንሰር ለማድረግ ለምትፈልጉ ትምህርቱን ለመማር የተሰናዱ ተማሪዎች ስላሉን በእኛ በኩል ልታገኙዋቸው ትችላላችሁ። ተመዝግበው ትምህርት ለመጀመር ከፈለጉ በዚህ የኢሜይል አድራሻ ያግኙን MYWONGEL@YAHOO.COM Calendar
|
